የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ከኤክሳይዝ ታክስ እና ከሱር ታክስ ነፃ ተደረጉ

ከውጭ የሚገቡም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የኤሌክትሪክ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች፣ የቤት አውቶሞቢሎች እና የዕቃ መጫኛ ተሽከርካሪዎች ላይ ዝቅተኛ የጉምሩክ ታሪፍ እንደሚጣልባቸው እና ከተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ከኤክሳይዝ ታክስ እና ከሱር ታክስ ነፃ እንደተደረጉ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። የገንዘብ ሚኒስቴር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኢንቨስትመንት ላይ የሚሰማሩ ኢንዱስትሪዎችን እና አስመጪዎችን የሚያበረታታ እንዲሁም ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ የታክስ ማሻሻያ ተግባራዊ መደረጉን አስታውቋል። […]

ኢትዮ ቴሌኮም ከአጠቃላይ ደንበኞቹ ሩብ ያህሉን የቴሌ ብር ተጠቃሚ ማድረጉን አስታወቀ

በሁለተኛው የሩብ ዓመት 6.27 ቢሊዮን ብር ትርፍ ከታክስ በፊት አግኝቷል ላለፉት 128 ዓመታት የአገሪቱን የቴሌኮም አገልግሎት በብቸኝነት ሲያቀርብ የቆየው ኢትዮ ቴሌኮም፣ ከ62 ሚሊዮን ደንበኞቹ ሩብ ያህሉን የቴሌ ብር ተጠቃሚ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ እስከተጠናቀቀው ሳምንት ድረስ ከ15.6 ሚሊዮን በላይ የሞባይል ገንዘብ ተጠቃሚ ደንበኞችን እንዳፈራ ያስታወቀው ኢትዮ ቴሌኮም፣ እነዚህ ደንበኞቹ በአገልግሎቱ ከ7.9 ቢሊዮን ብር በላይ ብር እንዲያዘዋውር ማስቻላቸውን […]