የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ከኤክሳይዝ ታክስ እና ከሱር ታክስ ነፃ ተደረጉ
ከውጭ የሚገቡም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የኤሌክትሪክ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች፣ የቤት አውቶሞቢሎች እና የዕቃ መጫኛ ተሽከርካሪዎች ላይ ዝቅተኛ የጉምሩክ ታሪፍ እንደሚጣልባቸው እና ከተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ከኤክሳይዝ ታክስ እና ከሱር ታክስ ነፃ እንደተደረጉ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። የገንዘብ ሚኒስቴር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኢንቨስትመንት ላይ የሚሰማሩ ኢንዱስትሪዎችን እና አስመጪዎችን የሚያበረታታ እንዲሁም ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ የታክስ ማሻሻያ ተግባራዊ መደረጉን አስታውቋል። […]