የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት ለልዩ ልዩ ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች ጎማዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

አዲስ ዘመን ( ሚያዝያ 20/2015 )
Closed: ግንቦት 08 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 ሰዓት

ግልጽ ጨረታ ቁጥር ት.መ.ማ.ማ.ድ/NCB/37/2015

ድርጅታችን ለ2015 በጀት ዓመት

  • ለልዩ ልዩ ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች ለስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዓይነት ጎማዎችን ከነውስጥ ላስቲኩ

በግልጽ ጨረታ ግዥ ቁጥር ት.መ.ማ.ማ.ድ/NCB/37/2015 ብቃት ያላቸው አስመጪ እና አከፋፋይ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ነጥቦች ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

  1. የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣ የታክስ ክሊራንስ ደብዳቤ ፣ የተ.እ.ታ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና የአቅራቢ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና ናሙና ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከትም/መሳሪ/ማም/ማከ/ድርጅት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋት 2:00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከ7፡30 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 35 መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  4. ጨረታው ግንቦት 08 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ በዚሁ እለት ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።
  5. ከላይ የተዘረዘሩትንና በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተመለከቱትን ግዴታዎች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።
  6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ Tel/ 011 646 3481 መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት