ዮቴክ ኮስትራክሽን ኃ.የተየግል ማህበር የሚሰሩ በጥሩ ሁኔታ የሚገኙ የኮንስትራክሽን ማሽኖች እና መኪኖች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

ሪፖርተር ( ግንቦት 13/2015 )
Closed: 25/09/2015 ዓ/ም ዓርብ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት

የጨረታ ማስታወቅያ

ዮቴክ ኮስትራክሽን ኃ.የተየግል ማህበር የሚሰሩ በጥሩ ሁኔታ የሚገኙ የኮንስትራክሽን ማሽኖች እና መኪኖች በሚገኙበት ገላን ፣ቃሊቲ ኪዳነ ምህረት ፣ ባቢሌ ፕሮጀክት እና ገላጎ ቴድሮስ ፕሮጀክት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

 1. ተጫራቶች የሚጫረቱትን ንብረት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 8 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን ዋና ቢሮ 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል የማይመለስ ብር 200 በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል
 2. ተጫራቶች ንበረቱ በሚገኘው ገላን እና ባሉበት ፕሮጀክት ቀርበው መመልከት ይችላሉ
 3. ማንኛውም በጨረታው ላይ የሚሳተፋ ተጫራቾች የተጠቀሱት ንብረቶች የጨረታው ማስከበሪያ (Bid Bond) ከምታቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 5% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ ከዋናው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል
 4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ዶክመንት ዉስጥ በተዘጋጀዉ የማጫረቻ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመመላት በታሽገ ፖስታ ዉስጥ አስገብተዉ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 13/09/2015 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት ቅዳሜን ጨምሮ 10 ተከታታይ የስራ ተናት ዉስጥ ዋናዉ መ/ቤት መግቢያ ላይ ባለዉ የእንግዳ መቀበያ አጠገብ በተቀመጠው ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል
 5. ጨረታው በቀን 24/09/2015 ዓ/ም ሐሙስ 11፡00 ሰአት ይዘጋል።
 6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅታችን ዋና መ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በቀን 25/09/2015 ዓ/ም ዓርብ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ካልተገኙ ጨረታው በጨረታ ኮሚቴና ታዛቢ ባለበት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
 7. ተጫራቶች የሚያቀርቡት ዋጋ ተ.እ.ታ /VAT/ ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡
 8. የመጫረቻ ዋጋ ቅዕ ላይ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ እና አሻሚነት ያለው የቁጥር አፃፃፍ ተቀባይነት የለውም
 9. ተጫራቶች ያስያዙት ሲፒኦ ካቀረቡት ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛሉ፡
 10. የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ክፍያውን ሙሉ በሙሉ ከፍለው ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል።
 11. የጨረታው አሸናፊዎች ክፍያ ከፈፀሙ በ10 ቀናት ውስጥ በራሳቸው ትራንስፖርትና ወጪ ንብረቱን ሙሉ በሙሉ ማንሳት ይኖርባቸዋል።
 12. የጨረታው አሸናፊዎች ክፍያ በተቀመጠው በ5 ቀናት የጊዜ ገደብ ካልከፈለ ጨረታው ውድቅ ሆኖ ለጨረታው ያስያዙት /bid bond/ ተመላሽ አይደረግም።
 13. በጨረታው ተሳታፊ ሆነው ጨረታውን ላላሸነፋ ተጫራቶች ለጨረታው ያስያዙት (Bid Bond) ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል።
 14. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ

አድራሻ፡- ዮቴክ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግል ማህበር ቫቲካን ፊት ላፊት ያለው መርየም ህንፃ እንገኛለን

የስልክ ቁጥር 011 557 3196/011 557 3198

ፋክስ 011 557 3187/011 557 3197

ኢ-ሜይል yotekconplc@gmail.com

አዲስ አበባ