የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት የፅህፈት መሳሪያዎች እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

አዲስ ዘመን ( ሚያዝያ 20/2015 )
Closed: ግንቦት 11/09/2015 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት

ለሁለተኛ ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር አፋ/ክ/ኤ/ግ/ጨ/ቁ/0003/2015

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአፋር ክልል ኤ/አ ፅ/ቤት በስሩ ለሚገኙ የስራ ከፍሎች እና ለማዕከላት አገልግሎት የሚውሉ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን /የስቴሽነሪ እቃዎችን/ ከዚህ የጨረታ ሠነድ ጋር በተያያዘው ዝርዝር መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም የስቴሽነሪ ዝርዝሮችን እንደሚከተለው እናቀርባለን።

ሎት የቢሮ መገልገያ እቃዎች (የፅህፈት መሳሪያዎች እቃዎች) የጨረታ ዋስትና የሚዘጋበት ቀን የሚከፈትበት ቀን
1 የኮምፒውተር ወረቀት A4 Size 30,000.00 ግንቦት 11 ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ሲሆን ግንቦት 11 ቀን ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ሲሆን
የፕሪንተር ቀለም 59A
የፕሪንተር ቀለም 37A
ቦክስ ፋይል

ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለ።

  1. ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ንግድ ፈቃድ የከፈለ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና ብቃት ያለው የንግድ ድርጅት በጨረታው መወዳደር ይችላል።
  2. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የገንዘብ ሚኒስቴር ምዝገባ የምስhር ወረቀት የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  3. የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ/ በመክፈል ሠመራ ከሚገኘው ካሸር ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 /ሠላሳ ሺህ/ EEU AFAR REGION አካውንት ቁጥር 10000-6875-95-48 ተከፋይ የሚሆን ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /C.P.O/ የባንክ ዋስትና ደብዳቤ /ባንክ ጋራንት/ ማስያዝ አለበት።
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በሠነዱ ባለው ፎርም ላይ በመሙላት ማቅረብ አለባቸው።
  6. ጨረታው ሚያዝያ 20/08/2015 ዓ.ም. በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለ በኋላ ግንቦት 11/09/2015 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ የውክልና ወረቀት የያዙ ወኪሎች በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን 10:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
  7. ለተጨማሪ ማብራሪያ አፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮ/ሎጅ/ዌር ሃውስና ፋሲሊቲ ቢሮ በስልክ ቁጥር 0987 01 74 91 ወይም 0911 05 53 04 በመደወል ወይም ቢሮ ቁጥር 16 በአካል ቀርቦ ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን በጨረታ ሠነዱ ላይ በተጠየቀው መሠረት የእቃውን ዓይነት በፎቶ የተደገፈ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  9. የአፋር ከልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት

ሠመራ