የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ከኤክሳይዝ ታክስ እና ከሱር ታክስ ነፃ ተደረጉ
ከውጭ የሚገቡም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የኤሌክትሪክ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች፣ የቤት አውቶሞቢሎች እና የዕቃ መጫኛ ተሽከርካሪዎች ላይ ዝቅተኛ የጉምሩክ ታሪፍ እንደሚጣልባቸው እና ከተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ከኤክሳይዝ ታክስ እና ከሱር ታክስ ነፃ እንደተደረጉ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። የገንዘብ ሚኒስቴር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኢንቨስትመንት ላይ የሚሰማሩ ኢንዱስትሪዎችን እና አስመጪዎችን የሚያበረታታ እንዲሁም ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ የታክስ ማሻሻያ ተግባራዊ መደረጉን አስታውቋል። […]
ክሊራንስ ለመስጠት ኦዲት የማያስፈልጋቸው አገልግሎቶች
ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት አገልግሎቶች ታክስ ከፋዩን ኦዲት ማድረግ ሳያስፈልግ የታክስ ክሊራንስ የምስክር ወረቀት ሊሰጥ ይችላል:- ንግድ ሥራ ፍቃድ ወይም የሙያ ፍቃድ ለማደስ፤ ጨረታ ለመካፈል ወይም ለመሳተፍ፤ ለተሽከርካሪዎች ወይም ለኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ዓመታዊ ምዝገባና ምርመራ (ክላውዶ) ለማድረግ፤ የባንክ ብድር ለማግኘት፤ የመድን ካሳ ለማግኘትና የተሽከርካሪ ሰሌዳ ለውጥ ለማድረግ፤ የድርጅት ስም ወይም አድራሻ […]