ድርጅት ማስተዋወቅ ምንድን ነው?

ማስተዋወቅ የግብይት አንዱ ዓላማ ሲሆን ምርትዎን ለገበያው ለማሳወቅ፣ ለማሳመንና ለማስገንዘብ የሚጠቀሙበት ነው፡፡ ማስተዋወቅን በሚገባ ማቀድ ለንግድዎ ስኬታማነት ወሳኝ

ነው፡፡

ለበርካታ ንግዶች የግብይት ግንኙነቶች የድርጅቱን ገጽታ የሚያንጸባርቁ ናቸው፡፡ ስለዚህም በግብይት ስልት የግንኙነት ኘሮግራሙ እንዴት ነው የሚታቀደው የሚለው በዋናነት ይካተታል፡፡ ይህን ለማከናወን የግንኙነት ኘሮግራሙ፣ የግብይትና የምርት ውህዶች ቅንጅትን ማጠናከር ያስፈልጋል፡፡

ይህ የግብይት ዓላማውን ለማሳካት ንግዱ የሚጠቀምባቸው የማስታወቂያ፣ የግለሰባዊ ሽያጭ፣ የሽያጭ ማስፋፊያ፣ የሕዝብ ግንኙነትና የቀጥታ ግብይት ውህድ ነው፡፡

ማስታወቂያ

ምርት/አገልግሎት ወይም ሀሳብ ላይ መሠረት አድርጎ በተለያዩ የግንኙነት መንገዶች (ሚዲያ) አማካኝነት በንግዱ የብዙኃን ግንኙነት የሚፈጠርበት ማንኛውም ክፍያ ያለው አቀራረብ ነው፡፡ ማስታወቂያ ድርጅቱን/ምርቱን/አገልግሎቱን በህትመት፣ በድምጽ ወይም በምስል ጥበብ አቀናብሮ ለማቅረብ የሚያስችል ነው፡፡ አንዳንዶቹም፡-

የማስተዋወቅ ዕቅድና ማዘጋጀት

    ውጤታማ የሆነ የማስታወቂያ ዘመቻ ሲያካሂዱ የሚከተሉትን ከግምት ማስገባት ያስፈልግዎተል፡-

  1. የትኩረት ገበያው ገለጻ፡-
  • የትኩረት ገበያዎ የቱ ነው?
  • የሚጠቀሙት ሚዲያ ምን ዓይነት ነው?
  • ለየትኛው የሚዲያ ኘሮግራም ትኩረት ይሰጣሉ?
  • ደንበኞች የማስታወቂያ መልዕክቱን እንዴት ነው የሚተረጉሙት?
  • ማነው ምርቱን ማስተዋወቅ ያለበት?
  1. የአጭርና የረዥም ጊዜ የግንኙነት (ኮምዩኒኬሽን)ዓላማዎች የግንኘነት ዓላማን ለማሳካት የትኩረት ገበያን ፍላጎት ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

የአጭር ጊዜ ዓላማዎች፡-

  • የትኪረት ገበያው ግንዛቤን ለመጨመር
  • በመጪዎቹ ሦስት ዓመታታ የሽያጭ መጠኑን ለመጨመር
  • ለተፎካባሪዎች ጥቃት ምላሽ ለመስጠት

ረዥም ጊዜ ዓላማዎች ምሳሌ፡-

  • በመጪዎቹ ሦስት ዓመታታ የገበያ ድርሻን ለማሳደግ
  • በመጪዎቹ (በቀጣዮቹ) ሦስት ዓመታታ ተጠቃሚ ያልሆኑትን ተጠቃሚ ለማድረግ
  • በመጪዎቹ (ቀጣዮቹ) አምስት ዓመታት የታማኝ ደንበኞች ቁጥር መጨመር
  1. መልዕክቱን የሚያስተላልፈው የግንኙነት መሣሪያ፡- መልዕክቱ ወደ ትኩረት ገበያው እንዲደርስ ተገቢውን የመልዕክት ማስተላለፊያ መንገድ መምረጥ ያስፈልጋል፡፡

መልዕክቱን ለመቅረጽ የሚከተሉት አራት ጉዳዮች  ላይ መወሰን ያስፈልጋል፡-

  • ምንድን ነው የሚባለው (ይዘቱ)?
  • እንዴት ነው የሚባለው ?
  • እንዴት ነው በስሜት ወይም በተምሳሌት የሚባለው (አቀራረብ)?
  • ማነው ሊለው የሚገባው?

የማስተላለፊያ መንገዱን ሲመርጡ የሚከተሉትን ነጥቦች ከግምት ማስገባት፡-

  • የሚዲያው ሽፋን ምንድን ነው? (በክልል፣ በሀገር አቀፍ…)
  • የትኛው ሚዲያ የበለጠ በትኩረት ገበያው ይመረጣል?
  • የማስታወቂያ በጀቱን ከግምት በማስገባት የትኛው ነው ተስማሚ?
  1. በጀት፡- በማስታወቂያ ዘመቻው በጀት መመደብ ይኖርቦታል፡፡ ይህም የግብይት ዓላማውን፣ የተፎካካሪዎች በጀትን፣ የተለያዩ ሚዲያዎች ወጪን፣ የድርጅቱ ጠቅላላ በጀትን ያገናዘበ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
  2. የግብይት ውህድን ማቀናጀት
  • የማስታወቂያው መልዕክት ከሌሎቹ ውህዶች (ዋጋ፣ ቦታና ምርት) ጋር የተጣጣመ መሆን አለበት፡፡
  • ተአማኒነት
  • ለአራቱ ውህዶች የተመደበውን በጀት ማመጣጠን
  1. እንዴት ነው የዘመቻው ውጤት የሚለካው፡- በዘመቻው ጅማሬ ያስቀመጧቸውን ዓላማዎች በመፈተሽ መለካት ይችላሉ፡-
  • ስለንግድ መለያው የተገኘው የግንዛቤ መጠን
  • የጨመረው የሽያጭ መጠን በፐርሰንት
  • የጨመረው የገበያ ድርሻ በፐርሰንት
  • የጨመረው ትርፈ በፐርሰንት

የግብይት ግንኙነት ዓላማን ለማሳካት የተለያዩ ቴክኒኮችን የያዘ አንድ ወጥ የማስተዋወቅ ስልት መቅረጽ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም ወጥነት ያለውን መልዕክት ማስተላለፍ ጠቀሜታ አለው፡፡

 የማስታወቂያ መለኪያዎች ዝርዝር

  • የባለፈው ዓመት የማስታወቂያ በጀቶችን ይመልከቱ
  • የማስታወቂያ ኘሮግራሙን ዓላማና መጠነ-ርዕይ ይወስኑ
  • ተደራሹን ይወስኑ
  • መልዕክቱንና ተያያዥ አቀራረቦችን ይቅረዱ
  • የማስታወቂያ ዘመቻውን የጊዜ ዝርዝር ይሥሩ፣ የቱን የማስታወቂያ ውህድ እንደሚጠቀሙም ይወስኑ
  • የማስታወቃያ (ኘሮሞሽን) በጀቱን ያስሉ
  • በተፈተሹ መስፈርቶች መሠረት የማስታወቂያ ማቴሪያሎችን ይቅረዱ
  • ዘመቻውን በይፋ ይጀምሩ
  • የማስታወቂያ ዘመቻውን ይገምግሙ
  • የሽያጭ መጠኑን ጨምሮታልን?
  • የትኩረት ገበያው ስለንግድዎ ያለውን ግንዛቤ ጨምሮታልን?
  • ብዙ ወጪ የማያስወጣ ነውን?

ጋዜጣ፡- ይህ የተማሩትን ደንበኞች ለመድረስ ይጠቅማል፡፡ ለምሣሌ የግል የጤና  ኮሌጆች በደንብ ለማብራራት በአዲስ አድማስ፣ ሪፖርተር፣ አዲስ ዘመን ጋዜጦች ያስተዋውቃሉ፡፡

  • ቴሌቪዥን፡- ይህ በድምጽና በእንቅስቃሴ ምርትዎት/አገልግሎትዎን እንዲገልጹ ያደርጋል፡፡ የበለጠ ብዙ ቦታዎች መታየት ቢችልም ውድ ነው፡፡
  • ቀጥታ መልዕክት፡- አንድ ውስን ደንበኛን ለመድረስ ይጠቀሙበታል፡፡ ለምሣሌ በኢትዮጵያ ቴሌኮምዩኒኬሽን አማካኝነት የሚላኩት የንግድ የተንቀሳቃሽ ስልክ መልዕክቶችን ማየት ይቻላል፡፡
  • መጽሔት፡- ከፍተኛ ጥራትና ቀለም ያለው ሕትመት ሲፈለግ ሁነኛ ተመራጭ ነው፡፡ ለምሣሌ በኢትዮጵያ የተለያዩ የመዋቢያ ንግዶች፣ የኮምፒውተር ማሰልጠኛ ተቋማት፣ የሙዚቃ ሱቆች፣ የአልባሳት መሸጫዎችና የመሳሰሉት እራሳቸውን/ምርታቸውን በቁም ነገር፣ ሮዝና በመሳሰሉት መጽሔቶች ያስተዋውቃሉ፡፡
  • ሬዲዮ፡- በዝቅተኛ ዋጋ ወደ ትኩረት ገበያው የሚያደርስ ነው፡፡ ለምሣሌ ኤቢሲ ድርጅት ማዳበሪያዎችንና የተሻሻሉ ዘሮችን በኢትዮጵያ በጠቅላላ ለሚገኙ ገበሬዎች የሚያቀርብ ሲሆን አዲስ ዓይነት ማዳበሪያ መጀመሩን ለገበያዎች መንገር ይፈልጋል ብንል በኢትዮጵያ ሬዲዮ መልዕክቱን ማስተላለፉ ተመራጭ ሊሆን ይችላል፡፡

Leave a Reply

Required fields are marked *