ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት አገልግሎቶች ታክስ ከፋዩን ኦዲት ማድረግ ሳያስፈልግ የታክስ ክሊራንስ የምስክር ወረቀት ሊሰጥ ይችላል:-
ንግድ ሥራ ፍቃድ ወይም የሙያ ፍቃድ ለማደስ፤
ጨረታ ለመካፈል ወይም ለመሳተፍ፤
ለተሽከርካሪዎች ወይም ለኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ዓመታዊ ምዝገባና ምርመራ (ክላውዶ) ለማድረግ፤
የባንክ ብድር ለማግኘት፤
የመድን ካሳ ለማግኘትና የተሽከርካሪ ሰሌዳ ለውጥ ለማድረግ፤
የድርጅት ስም ወይም አድራሻ ለመለወጥ፤
የንግድ ሥራ ሀብት መቀነስን ሳይጨምር የንግድ ዘርፍ ቅነሳ ለማድረግ፤
ድርጅቶች እንደገና ተደራጅተው ሲዋሀዱ የተዋሀደውን ድርጅት የታክስ ዕዳ አካቶ የሚዋሃዱ ስለመሆኑ የፀደቀ ሰነድ ለማቅረብ፤በሌላ በኩል፡-1. የክሊራንስ ጥያቄ በቀረበበት ጊዜ የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ የተሰጠው እና ያልተከፈለ የታክስ ዕዳ ያለበት ታክስ ከፋይ ኦዲት ሳይደረግ የባንክ ብድር እንዲወስድ ክሊራንስ የሚሰጠው ዕዳውን የከፈለ እንደሆነ ወይም ለመክፈል የባንክ ዋስትና ያቀረበ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡2. ታክስ ከፋዩ የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ሊሰጠው የሚችለው:- ታክስ ከፋዩ ዓመታዊ የንግድ ትርፍ ግብር ማስታወቂያ እና መክፈያ የመጨረሻ ቀን ከመድረሱ በፊት የንግድ ሥራ ፍቃድ ለማደስ፣ በጨረታ ለመሳተፍ፣ የባንክ ብድር ለመውሰድ እና የጉዳት ካሳ ለማግኘት የሚቀርብ የታክስ ክራንስ ምስክር ወረቀት ጥያቄ ከሆነ ጥያቄው ከቀረበበት የግብር ዘመን በፊት ታክሱን አስታውቆ ግዴታውን የተወጣ ስለመሆኑ እና የታክስ ክራንስ ምስክር ወረቀት የተጠየቀበትን አገልግሎት ዓይነትና የተፈለገበትን ምክንያት የሚያስረዳ ማስረጃ ሲያቀርብ ብቻ ይሆናል፡፡3. የባንክ ብድር ለማግኘት የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት እንዲሰጠው ለጠየቀ ሰው የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት የሚሰጠው ጥያቄ አቅራቢው የንግድ ሥራ ያልሠራና በግብር ከፋይነት ያልተመዘገበ ከሆነ ከታክስ መስሪያ ቤቱ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ከመረጃ ቋት ተገቢውን ማጣራት አድርጎ ጠያቂው በንግድ ሥራ አለመሠማራቱን በማረጋገጥ ይሆናል፡፡4. የንግድ ሥራ ፍቃድ ለመመለስ ጥያቄ ሲያቀርቡ ከታክስ ሚኒስቴሩ የሥራ ክፍሎች እና ከሶስተኛ ወገን በማጣራት የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት የሚሰጥ ይሆናል፡፡